ኣመጣጣችን

የኢንስቲትዩቱ ኣጠቃላይ መግለጫ

የትግራይ ጥናትና ምርምር ፖሊሲ ኢንስቲትዩት በኣዋጅ ቁጥር 306/2018 በትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት ተkቁሞ በፖለቲካዊ፣ ቁጠባዊ፣ ማሕበራዊ ጉዳያዮች እና ቴክኖሎጂ መሰረት ያደረገ ምርምር በማካሄድ በፖሊሲና እስትራቴጂ አልሞ መፍትሄና ምክር ለመንግስት ያቀርባል፡፡ ተkሙ በዋናነት የሚተገብራቸውና የሚያስተባብራቸው ምርምሮች፦ መልካም አስተዳደርን ማስፈን፣ ግብርናና የገጠር ልማትን ማጎልበት፣ የከተማና ኢንዱስትሪ ዕድገት ማረጋገጥ እና ለግልጋሎት ሰጪ አካላትን የዓቅም ግንባታ ስራዎች ማካሄድ ናቸው፡፡ ኢንስቲትዩቱ በክልላዊና አገራዊና የፖሊሲና ሌሎች ተዛማጅ ምርምሮችን አርአያ የምርምር ተkም ሁኖ የማየት ግብ አንግበዋል፡፡ የትግራይ ጥናትና ምርምር ፖሊሲ ኢንስቲትዩት የማሕበረ ቁጠባዊ ፍላጎቶች መሰረት ያደረጉ የፖሊሲ ጥናትና ምርምር ለማካሄድ እንዲችል በአራት እስትራቴጂያዊ ዘርፎች ተዋቅረዋል፡፡ እነዚህ ዘርፎችም በንኡሳን ቡድኖች የተዋቀሩ ናቸው፡፡